ግፍም መጠን አለው ነውርም ልክ አለው።

ከምንተ ንግበር አባል
ከዶ/ር ፍቅርተ የተወሰደ!

“ወገኖቼ:-
ግፍም መጠን አለው – ነውርም ልክ አለው።
ለእኛም ደግሞ መደንዘዝም አይነት አለው።
የተደቀነብን አደጋ ግዙፍ ነው – አሁን እያየን ያለነው የበረዶውን ግግር ተራራ ጫፍ ብቻ ነው።
ይበቃል!
የሚያበቃው ደግሞ እኛ ተደራጅተን ተቀናጅተን ለህልውናችን ለሰው ልጅ ልዕልና ለክርስቶስ ቤተክርስቲያን ክብር የቆምን እንደሆን ብቻ ነው::
በያለንበት እግዚአብሔር በሰጠን መክሊት እንትጋ- በየአጥቢያችን ምዕመኑን እናደራጅ፤ በየሰፈራችንም በቤተሰባችንም እንዲሁ – አንድም ሰው ሊያበረክተው የሚችለውን አስተዋጽዖ አይናቀው – አንድ ሰው ብዙ ተፅዕኖ መፍጠር ይችላል:: ግፍ የሚበረታው በግፍ አድራጊዎች ብርታት አይደለም – በበጎ ሰዎች ዝምታና ቸልታ ነው:: ዝም ካልን ነገ ይብሳል- የእያንዳንዳችንንም በር ያንኳኳል:: ለእውነት እንቁም – ለግፉዓን ድምፅ እንሁን- እሴቶቻችንን ከፍ እናድርግ::
በአካል ተገናኝቶ መወያየት እና የሥራ ድርሻ መውሰድ መልካም ነው – የሚተዋወቁ የሚተማመኑ ሰዎች ቡድን እየመሰረቱ ይተጋገዙ:: ሥራና የቡድን አደረጃጀትን ግን በአካል ብቻ!
እንድንወያይ የፈቀደልን አምላክ የተመሰገነ ይሁን፤ በያላችሁበት በጸሎት አስቡን!”

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.